የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ላይ ምክክር እየተደረገ ነዉ፡፡

Ethiopia : የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርአትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመው የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ ሲሆን÷ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሩን ጨምሮ፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የበላይ አመራሮች ተገኝተዋል።

የግንኙነት መድረኩ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ታዲያ ይህ አዋጅ ቁጥር 1231 ምን ምንን ይዟል ለሚለው የበለጠ መረዳት እንዲያስችላችሁ አያያዝኩላችሁ

Share this:
Ayalew Bitane
Ayalew Bitane
Articles: 27

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *