
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ላይ መሆኗ በማስታወስ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋትና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽንና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
- ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፦
• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)
• ኮምፓስ (Compass)
• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS) - ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች ፦
• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)
• ሳተላይት ስልክ (satellite phone) - ቪሳት እና ቢጋን (A very small aperture terminal (VSAT) and Broadband Global Area network (BGAN))
- ድሮኖች (Drones)
እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ እንደሚጠበቅበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳውቋል።