የፍርድ ቤቶች የክረምት የእረፍት ጊዜ ተጠናቆ ወደ መደበኛ ሥራችን ስንመለስ፣ እኛ የሕግ ባለሙያና ጠበቆች ትልቅ የሙያና የዜግነት ኃላፊነት ይጠብቀናል።
ጠበቃነት የደንበኞችን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ የፍትሕ ሥርዓቱ ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ እውነተኛና አሳታፊ እንዲሆን የማድረግ ታላቅ ማህበራዊ አደራ ነው። በሕግ የበላይነት ሰፍኖ ማየት ለሁላችንም ሰላም፣ እድገት እና ዋስትና መሰረት ነው።
በዚህ አዲስ የሥራ ዘመን፡
🇪🇹ሕግንና አሠራርን በማስከበር የፍትሕ ሥርዓቱ እንዲጠናከር የእለት ተእለት ሙያዊ አስተዋፅኦ ማድረግ፣
🇪🇹የደንበኞቻችንን መብት በቅንነትና በታማኝነት መሞገት፣
🇪🇹ከፍርድ ቤቶችና ከሕግ አካላት ጋር በሙያዊ ሥነ-ምግባር በመተባበር ፍትሕ ሳይዘገይ እንዲሰጥ ተገቢውን ጥረት ማድረግ፣
ቀዳሚ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ።
ፍትሕን እንዲሰፍን በሚደረገው በዚህ መልካም ጉዞ ላይ ለምትገኙ ባልደረቦቼ፣ ዳኞች፣ ዐቃቢያነ ሕግ እና ሙሉ የፍትሕ አካላት እንኳን ለ2019 የሥራ ዘመን አደረሳችሁ!
መልካም፣ ውጤታማ እና የፍትሕ ዘመን ይሆንልን ዘንድ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ🙏🙏🙏
አያሌው ቢታኔ (የሕግ አማካሪና ጠበቃ)
#የሕግየበላይነት #ፍትሕ #ኢትዮጵያ #ጠበቃ #Ethiopia #LegalProfession #AyalewBitane


